አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና ኮሙኒኬሽንና ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) የኢትዮጵያን ከተሞች በማዘመን የተጫወተውን ሚና አደነቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤይጂንግ ቆይታቸው ከሲሲሲሲ ጋር ከጥቂት ወራት በፊት የተጀመረውን ውይይት ዛሬ ቀጥለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሲሲሲ የኢትዮጵያን ከተሞች በማዘመን የተጫወተውን ሚና ማድነቃቸውን የገለጸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ፤ ከቻይና ጭምር የሌላ ሀገራት ቱሪስቶችን በሰፊው የመሳብ ትልም እውን ለማድረግ ሆቴሎችን፣ አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን መገንባት ቁልፍ እንደሆነ ማውሳታቸውን ገልጿል።