የሀገር ውስጥ ዜና

ፋውንዴሽኑ የሕክምና ግብዓት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

By Melaku Gedif

September 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አመራሮች ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ሊቀ መንበር ቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በመድረኩ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር)÷የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት የመረጃ ስርዓቱ ግልፀኝነት ያለውና ተደራሽነቱ የተረጋገጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሠለቱን ለማጠናከር ባደረገው የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ የተሠሩ በርካታሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ምክክር ተደርጓል፡፡

ማህበረሰቡ ከሕክምና ግብዓት አቅርቦቱ ተጠቃሚ እንደሆነና የመድሃኒት ብክነት መጠን በእጅጉ እንደቀነሰ መገለጹን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የግብዓት ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥም የሥርጭት ሒደቱ ላይ ትብብር እንደሚደረግ የፋውንዴሽኑ መስራች ቢል ጌትስ ተናግረዋል፡፡