አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሐረር ከተማ የምስራቅ ዕዝን የ47 ዓመታት ጉዞ የሚዘክረውን ሙዚዬም ጎብኝተዋል፡፡
በ1979 ዓ.ም የተቋቋመ የምስራቅ ዕዝ ሙዚዬም ለረጅም ዓመታት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ የቆየና በዕዙ ድጋፍ ለጉብኝት ክፍት የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በጉብኝቱ በሶማሊያ ወረራ ወቅት የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ለማስጠበቅ የምስራቅ ዕዝ የተጠቀማቸው ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
ከሶማሊያ ጦር የተማረኩ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች፣ ታንኮች ፣ የሙዚቃና የስፖርት ትጥቆችን ጨምሮ የዕዙን የ47 ዓመታ ታሪክ የሚገልፁ ቅርሶች መጎበኝታቸውንም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡
በጉብኝቱ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰና ጀኔራል ጌታቸው ጉዲናን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና የሃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል።