አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ መሀመድ አብዲ ዋሬ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸውም ፥ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ግንባታ ላይ ድጋፍ የማድረግ፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የመከላከል እና በቀጣናው ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ያለመ እንደሆነ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።