Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ባለሃብቶችን ለመሳብና ለኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት የባለድርሻ አካላት የጋራ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ውይይቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው እያለሙና ለማልማት ፍላጎት ያሳዩ ባለሀብቶችን እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን በቀጥታ ለማገናኘት ያለው ነው ተብሏል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ የተነገረ ሲሆን÷ በፓርኮቹ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ባለሃብቶችን ለመሳብና ለኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም በውይይቱ ተገልጿል።

በፎረሙ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በቅድስት አባተ

Exit mobile version