Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በፋፈን ዞን የመንገድ ፕሮጀክት መረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በክልሉ ፋፈን ዞን የመንገድ ፕሮጀክት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

የቀብሪበያህን ወረዳ ከቡለደሪ ቀበሌ ጋር የሚያገናኘው የጠጠር መንገድ ፕሮጀክት 56 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ በመንግስት በተመደበ 153 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው መሆኑ ተገልጿል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ሀገራዊ ለውጡ እውን ከሆነ በኋላ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ፕሮጀክቶች መከናወናቸውን  ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአካባቢው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሰረታዊ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version