Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 1 ሺህ 754 የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርት የደበቁና ለሕግ ተገዥ ያልሆኑ 1 ሺህ 754 የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አስር ኢብራሂም አስታወቁ፡፡

በቅርቡ ተግባራዊ የሆነውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ በሕገ-ወጥ የንግድ ተግባር በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት፡፡

እስከ አሁን የገበያውን ጤናማነት ለመቆጣጠር ከተቋቋመ ግብረ-ኃይል ጋር በተደረገ ክትትል ምርት የደበቁና ያልተገባ ዋጋ የጨመሩ 1 ሺህ 754 የንግድ ተቋማት እንዲታሸጉ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል የሥድስት ድርጅቶች ፈቃድ መሠረዙን፣ የ11 ድርጅቶች ንብረት መወረሱን እና 57 ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ ተደጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለመጪው አዲስ ዓመትም የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በበቂ ሁኔታ ለሸማቹ እየተሰራጩ ነው ብለዋል፡፡

Exit mobile version