አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳድ ሙባረክ አል ናይሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው፤ ኢትዮጵያ እና ኳታር በኢኮኖሚ እና ቢዝነስ ዲፕሎማሲ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ በሚያጠናክሩባቸው መስኮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት እኩል ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ሌሎች መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡