Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበልና ላካሄድነው ጠቃሚ ውይይት አመሰግናለሁ ብለዋል።
ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ዘርፈብዙ ድጋፍ በእጅጉ ታደንቃለች ሲሉም ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር የተለያዩ ተግዳሮቶችን ብናስተናግድም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ትርጉም ያላቸው የለውጥ ርምጃዎች ተራምደናል ነው ያሉት።
በዚህ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና መጫወታቸውንም አስገንዝበዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በቱሪዝም ብሎም በወረቀት እና ፐልፕ ያሉ ተያያዥ ግብዓቶች ኢንዱስትሪን ለማሳደግ እምቅ አቅም መኖሩን አውስተው÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በጽናት እንሰራለን ብለዋል።
Exit mobile version