Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ  ለአልሚዎች አዳዲስ ዕድሎች መክፈታቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያደረገቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለአልሚዎች አዳዲስ ዕድሎች መክፈታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ አስገነዘቡ፡፡

በቤጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮ-ቻይና ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም ላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር÷ ቻይና የምትከተለውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ኢትዮጵያ ታደንቃለች ብለዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ እንደምትሠራ አረጋግጠው÷ የምትገኝበት ቁልፍ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሥፍራ ከማዕድን ሀብት እና ከአላት የሰው ሃብት አቅም ጋር ተደምሮ ተፈላጊቷን ከፍ እንደሚደርገው አብራርተዋል፡፡

በሁሉን አቀፍ ትብብር ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን በመግለጽ÷ ቻይናውያን አልሚዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቀርበዋል፡፡

ከለዚህም የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን አስታውቀው ማሻሻያዎቹ  ኢንቨስትመንትን የሚያበረታቱና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

Exit mobile version