አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላምና ጸጥታ ሥራዎችን በእቅድ እና በተደራጀ መንገድ መስራት ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ከዞን እና ልዩ ወረዳ አመራሮችእንዲሁም ጸጥታ አካላት ጋር በክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
በውይይት መድረኩ እንዳሉት÷ በክልሉ ሁሉም የልማት ሥራዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲከናወኑ ቅድሚያ ለሰላምና ጸጥታ መስፈን ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል።
ቀጣይ ህዝባዊ በዓላት ያለ ምንም ችግር እንዲከበሩ የክልሉ መዋቅር በእቅድና በተደራጀ መንገድ መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበዋል።
የጸጥታ ችግር ምልክቶችን ቀድሞ ማጥናት እንደሚገባ ጠቁመው÷ ለዚህ ስኬትም ክልላዊና ሀገራዊ የሰላምና ጸጥታ ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ መጠቆማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡