Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክልሉ መንግሥት የልማት ድርጅቶች የሕዝቡን ተጠቃሚነት እንዲያጎለብቱ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የልማት ተግባራት ላይ ተሳትፏቸውን በማጠናከር የሕዝቡን ተጠቃሚነት እንዲያጎለብቱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን አሳሰቡ።

ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ እንዳሉት÷ የልማት ድርጅቶች በተያዘው በጀት ዓመት የክልሉን የልማት እድገት ለማፋጠን በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው።

በየተሰማሩበት የልማት ዘርፍ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ተግባራት ላይ በንቃት በመሳተፍ የሕዝቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተሳትፏቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት፡፡

በነበረው ችግር ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶችን በአዲስ መልክ በመገንባትና በመጠገን ለአገልግሎት በማዋል አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም እያንዳንዱ ድርጅት በዕቅድ በማካተትና በጀት በመመደብ የክልሉ መንግሥት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት መፈጸም እንደሚጠበቅበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሥራ ዕድል ፈጠራና ሌሎች ተግባራት በንቃት በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

Exit mobile version