Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ረገድ አበረታች ስራ እየሰራች መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ፖል አንቶኒ ሀንዲሊን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ምስጋኑ ÷ መንግስት በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች እያደረገ ላለው ድጋፍ የመንግሥታቱ ድርጅት ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና ሌሎች የረድኤት ተቋማት አጋርነት ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፖል አንቶኒ በበኩላቸው÷ የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠረውን ቀውስ ለመከላከል እና ለመቋቋም በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን የአረንጓዴ ዓሻራ መርሐ ግብር፣የሴፍትኔት ፕሮግራም እና ብሔራዊ የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አድንቀዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ መንግሥት እና በተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version