አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
አቶ አሻድሊ ሀሰን በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በሚያደርጉት አስደናቂ ድጋፍ ግድቡ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
የክልሉ ሕዝብና መንግሥትም ለግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የሕዳሴ ግድብ 3ኛው እና 4ኛውን ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ማብሠራቸው በሕዝብ ዘንድ ትልቅ ደስታ መፍጠሩንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።