አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ሲያከናውነው የነበረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ አጠናቋል።
የክልሉን አጀንዳ ያደራጁ ወኪሎችም አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክሩ አስረክበዋል።
በሲዳማ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ከአምስት ባለድርሻ አካላት የተወከሉ ከ1ሺህ 800 በላይ ተሳታፊዎች በሂደቱ ተካፋይ መሆን ችለዋል።
ባለፉት ሰባት ቀናት የተከናወነው ይህ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት አሳታፊ እና አካታች እንደነበር ነው ተሳታፊዎች የተናገሩት።
በፍቅርተ ከበደ፣ ጀማል ከዲሮ እና ታመነ አረጋ