አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ መስራችና ሊቀ መንበር ባለሃብቱ ቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል።
ቢል ጌትስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እና ከብሔራዊ መታወቂያ ዲጂታል ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ጋር ባደረጉት ፍሬያማ ውይይት፤ ያለውን አጋርነት ማጠናከር ስለሚቻልበት ሁኔታና የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነት ላይ መክረዋል።
በተለይም ቀጣናዊ፣ ስርዓተ ጾታ እንዲሁም ኢስላሚክ ፋይናንስን ማስፋፋት ላይ መወያየታቸውን የብሔራዊ ባንክ መረጃ አመልክቷል።
ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ መንግስት የዲጂታል መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የዲጂታል ሽግግርና የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ቢል ጌትስ አረጋግጠዋል።