የሀገር ውስጥ ዜና

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መሪ ሃሳብ ይፋ ሆነ

By Shambel Mihret

September 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ የበዓሉን መሪ ሀሳብ ይፋ አድርጓል።

ኮሚቴው ባካሄደው ውይይት 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል «ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት» በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚከበር አስታውቋል።

በውይይቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር÷ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች ለማስከበር፣ ብዝኃነት እንዲጠናከር፣ አብሮነትና ወንድማማችነት ሥር እንዲሰድና ጤናማ የፌዴራል ሥርዓት እንዲጎለብት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀኑ ሲከበርም ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር የዜጎችን ሕብረብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር መንገድ መሠራት አለበትም ማለታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡