አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ተጀምሯል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)÷ ምክክርን ባህል በማድረግ የልዩነት ምንጭ የሆኑ አለመግባባቶችን፣ ጦርነትና ግጭቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተመካክሮ መፍታት ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል::
ለሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን ጨምሮ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡