አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጪው አዲስ አመት በዓል የሚሆኑ የፍጆታ ዕቃዎች በስፋት መቅረባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶችን ጨምሮ የእንስሳት ተዋፅዖዎች በበቂ ሁኔታ ቀርበዋል ብለዋል፡፡
በእሁድ ገበያዎች እና የገበያ ማዕከላትም እስከ በዓሉ ድረስ ግብዓቶች በስፋት እንደሚቀርቡ ጠቁመው÷ በከተማዋ ባሉ የገበያ ማዕከላት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ድረስ የሚቆይ ባዛር መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
በዓሉን ምክንያት በማድረግም ምርት እንዳይደበቅና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ አሳስበዋል፡፡
በቅድስት አባተ