የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጥላሁን ከበደ ከክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤት አባላት ጋር እየመከሩ ነው

By Feven Bishaw

September 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከፍተኛ አስፈጻሚ አካላት ከክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤት አባላት ጋር ሁለተኛ ዙር ክልላዊ የማጠቃለያ ውይይት በወላይታ ሶዶ ከተማ እያካሄዱ ነው፡፡

የምክር ቤቶቹ አባላት ላለፉት ሦሥት ሳምንታት በክልሉ ሁሉም ዞኖች ከመራጩ ህዝብ እና ከየዞኑ አስፈጻሚ አካላት ጋር በተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ሲያካሂዱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

በውይይቶቹ የተነሱ የተለያዩ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች እና በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ደግሞ ዛሬ ከርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደና ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አስፈጻሚ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

መድረኩ በየአካባቢው ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመለየትና ደረጃ በደረጃ ምላሽ በሚያገኙበት አግባብ ዙሪያ በጋራ በመምከር የክልሉን ህዝቦች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በማቴዎስ ፈለቀ