አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተለያዩ የግብርና መስኮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ሊቀመንበር ቢል ጌትስ ተፈራርመዋል፡፡
ሁለቱ ሃላፊዎች በተለይም በወተትና ወተት ተዋፅኦ፣ በዶሮ እርባታና በምርጥ ዘር ምርምር ላይ ትኩረት አድርገው በጋራ ለመስራት ነው ስምምነት ላይ የደረሱት።