Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሲደረግ የነበረው የአጀንዳ ልየታ የምክክር መርሐ ግብር መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በክልሉ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ በነበረው የአጀንዳ ልየታ መርሐግብር ከ82 ወረዳዎች የመጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች ተሳትፈዋል፡፡

የህብረተሰብ ክፍሎቹን ወክለው በአጀንዳዎቻቸው ላይ ሲወያዩ የቆዩት ከ1ሺህ 400 በላይ ተሳታፊዎች ከነገ ጀምሮ በሚኖረው የባለድርሻ አካላት ምክክር ላይ የሚሳተፉ 80 ወኪሎችን በመምረጥ ነው መርሐግብሩ የተጠናቀቀው፡፡

የተመረጡት ተወካዮችም ከነገ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከባለድርሻ አካላት ጋር አጀንዳዎቻቸውን የጋራ በማድረግ የክልሉን አጀንዳ የሚያደራጁ ይሆናል መባሉን የምክክር ኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

Exit mobile version