የሀገር ውስጥ ዜና

ምግብ ዋስትና ሥራ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ሳትበገር ራሷን እንድትችል በር ይከፍታል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)(ዶ/ር)

By Mikias Ayele

September 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምግብ ዋስትና ሥራ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ሳትበገር ራሷን እንድትችል በር ይከፍታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ሥራዎች እና የምግብ ሉዓላዊነት መንገድ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ሳትበገር ራሷን ችላ ለምትቆምበት መጻዒ ተስፋ በር የሚከፍትነው ብለዋል፡፡

በዘላቂ የግብርና ሥራ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ሥራ ኢትዮጵያ ምርታማነትን ማላቅ፣ የአዝርዕት አይነትን ማብዛት ብሎም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ማሻሻል ትችላለች ነው ያሉት።

መሰል ትብብሮች የማኅበረሰብን አቅም ከፍ  እንደሚያደርጉ፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንደሚከፍቱ እና ፈጠራን እንደሚያበረታቱ  አስገንዝበዋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያን በዘላቂ የምግብ ሥርዓት መሪ ያደርጋታል ፤የበለፀገ የምግብ ዋስትና የተረጋገጠበት መፃዒ ጊዜንም ለህዝባችን ያረጋግጣል ሲሉም ገልጸዋል፡፡