Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ላጡ ዜጎች የ40 ቀን መታሰቢያና ከአደጋው የተረፉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያግዝ የገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሁም አደጋውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ላደረጉት ድጋፍ የምስጋና መድረክ ነው በመዲናዋ በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡

የድጋፍ ማሰባሰቢያና የምስጋና መድረኩ በጎፋ ልማት ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የጎፋ ዞን ተወላጆች አደጋውን ተከትሎ መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት ድጋፍና ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘው ተሻገር፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ሌሎችከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመራኦል ከድር

Exit mobile version