Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ-ቴሌኮም ለጎፋ ዞን ከ 11 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ-ቴሌኮም በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ከተቋሙና ከህብረተሰቡ የሰበሰበውን ከ 11 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ፋስሊቲስ ኦፊሴር አቶ አይናለም አልበኔ በአደጋው በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

ተቋሙ በአደጋው የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን መልሶ ለማቋቋም 8091 አጭር ኮድ እና በቴሌ ብር መተግበሪያ ለህብረተሰቡ ይፋ በማድረግ ከህብረተሰቡ ገንዘብ እያሰባሰበ መቆየቱን ገልጸው በሂደቱም እስካሁን 1 ሚሊየን 352 ሺህ 843 ብር ከ 25 ሳንቲም መሰብሰቡን ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ(ኢ/ር) ÷ ኢትዮ-ቴሌኮም ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ተረጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ጳጉሜን 1 በአንድ ጀምበር ከ 200 በላይ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ የንቅናቄ ሥራ እየተሠራ መሆኑን መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version