የሀገር ውስጥ ዜና

የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር የመንገድ ክፍል ከትራፊክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ቀናት ዝግ ሆኖ ይቆያል

By Meseret Awoke

August 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር የመንገድ ክፍል ከትራፊክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ቀናት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ በባሌ ዞን በሮቤ-ጊኒር መስመር ከጋሰራ መገንጠያ ኪሎ ሜትር 30 ላይ የሚገኘው የደንበል ወንዝ የብረት ድልድይ ከባድ ጭነት በጫነ ተሸከርካሪ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ ተገቢውን የጥገና ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሶ፥ ስራው እስኪጠናቀቅ የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር የመንገድ ክፍል ከትራፊክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ቀናት ዝግ ሆኖ እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የጥገና ስራው ተጠናቆ ድልድዩ ለትራፊክ ክፍት እስኪደረግ ድረስ አሽከርካሪዎደች የሮቤ-ጎሮ-ጊኒር እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡

ስራውን በአጭር ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑንም አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡