የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምክክር መድረክ በይፋ ተጀመረ

By Shambel Mihret

August 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)÷ኮሚሽኑ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱን ለሀገር የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን መለየት ባስቻለ መልኩ በግልጽነትና በአሳታፊነት እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዛሬ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረው የምክክር መድረክም ለኢትዮጵያ መፃኢ ወሳኝ ጉዳዮች የሚለዩበት ይሆናል ብለዋል።

በምክክር የማይፈታ ነገር የለም ያሉት ኮሚሽነር ዮናስ÷ታሪካዊ ምዕራፉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድምፅ የሚሰማበትና የመፍትሄ አማራጮች ይበልጥ የሚደመጡበት እንደሆነም መናገራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለስድስት ቀናት በሚቆየው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምክክር መድረክ በክልሉ ከሚገኙ 82 ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት እና የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎችን ጨምሮ ከ1 ሺህ 700 በላይ ተወካዮች ይሳፋሉ ተብሏል፡፡