አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ሙያዎች ላይ የሚሰራ “የዘርፍ ክህሎት ካውንስል” ተቋቁሞ በይፋ ሥራ ጀምሯል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)÷ ካውንሱሉ በክህሎት ልማት ሥራዎች በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ የሚታየውን የገበያ አቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት ለመለየት ያስችላል ብለዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ ክፍተቱን የሚሞላ እና ገበያው የሚፈልገውን የበቃ የሠው ሃይል ልማት አቅርቦት ላይ በትኩረ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
ካውንስሉ በኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፍ በአይነቱ አዲስ መሆኑን ጠቁመው÷ ካውንስሉን ለማቋቋም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ተሞክሮ መወሰዱን ጠቅሰዋል፡፡
ከመንግስት አራት ተቋማትን በማካተት የተቀሩት በአግሮ ፕሮሰሲንግ ከተሰማሩ የግሉ ዘርፍ፣ ከአሰሪ እና ከዘርፍ ማህበራት በድምሩ 17 ተቋማት አካቶ መቋቋሙን ገልጸዋል።
ካውንስሉ በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ የሚፈልገውን የሰው ሀይል፣ ቴክኖሎጂና ክህሎት ለይቶ ለክህሎቱ የሚሆን የስልጠና ሰነድ የሚያዘጋጅ መሆኑንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡