አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን ከምዕራባውያን በድጋፍ ካገኘቻቸው ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች መካከል አንዱ ለሩሲያ ጥቃት ምላሽ በሚሰጥበት ወቅት መከስከሱን አስታውቃለች፡፡
ዩክሬን በቅርቡ የመጀመሪያዎቹን አሜሪካ ሰራሽ ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ከምዕራባውያን በድጋፍ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡
ሚሳኤል፣ ቦምብና ሮኬቶችን የመሸከም አቅም አላቸው የተባሉት ተዋጊ ጄቶቹ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጦርነት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርጉ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በወቅቱ ተናግረው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ዩክሬን ከተረከበቻቸው ተዋጊ ጄቶች መካከል አንዱ ከአራት ሳምንታት ቀይታ በኋላ ለሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት ምላሽ በመስጠት ላይ እያለ መከስከሱ ተነግሯል፡፡
የኤፍ-16 ተዋጊ ጄቱ አብራሪ ኦሌክሲ ሜስ ለጥቃቱ አጸፋዊ ምላሽ በመስጠት ላይ እያለ መሰዋቱንም የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡