ቢዝነስ

2 ነጥብ 66 ሚሊየን ቶን ገቢ ምርት በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉ ተገለጸ

By Feven Bishaw

August 30, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 66 ሚሊየን ቶን ገቢ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 1ነጥብ 27 በሚሊየን ቶን ገቢ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ታቅዶ ነው 2 ነጥብ 66 ሚሊየን ቶን ምርት መተካት የተቻለው፡፡

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ እንዲሁም ኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች የእቅዳቸውን መቶ በመቶ በላይ ማሳካት መቻላቸው ተጠቁሟል፡፡

የምግብና መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ደግሞ የእቅዳቸውን 90 በመቶ ማሳካት መቻላቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡