የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የታክስ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

By amele Demisew

August 30, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የታክስ ንቅናቄ እና የግብር ከፋዮች የእውቅናና ምስጋና መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው።

ንቅናቁው”ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ-ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ አስካለ አልቦሮና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ግብር ከፋዮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ የ2017 የታክስ ንቅናቄ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን÷በ2016 በጀት ዓመት ግብር በመክፈል ሃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት ዕውቅ እንደሚሰጥም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡