ስፓርት

ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው 4 የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ

By Melaku Gedif

August 30, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፔሩ ሊማ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው አራት የፍጻሜ ውድድሮችበዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ፡፡

በዚህ መሰረትም አትሌት ሕይወት አምባውና አትሌት ብርሃን ሙሉ የሚሳተፉበት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ርምጃ ውድድር ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ25 ላይ ይካሄዳል፡፡

በወንዶች 800 ሜትር ደግሞ አትሌት ጀነራልብርሃኑ ኢትዮጵያን በመወከል ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ35 ላይ ይወዳደራል፡፡

እንዲሁም በሴቶች 800 ሜትር አትሌት አስቴር አሬሪ ከሌሊቱ 6 ሰዓት 50 በፍጻሜው ውድድሩ እንደምትሳተፍ የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሌሊቱ 7 ሰዓት 45 ደግሞ አትሌት አለሽኝ ባወቀ እና አትሌት ማርታ አለማየሁ በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር ሀገራቸውን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅና በሁለት ብር በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት አንደኛ ደረጃን ይዛለች።