የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

By Meseret Awoke

August 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር) ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት  እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር)÷በፍልስፍና መምህርነት፣ በተመራማሪነትና በአማካሪነት አገልግለዋል፡፡