Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰራዊቱ በሶማሊያ የከፈለው መስዋዕትነት ለቀጣናው ሰላም መፈጠር ሁለንተናዊ ድርሻ ነበረው – ሜ/ጄ አዳምነህ መንግስቴ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ48ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በሶማሊያ የከፈለው መስዋዕትነት ለቀጣናው ሰላም መፈጠር ሁለንተናዊ ድርሻ እንደነበረው የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ ገለጹ፡፡

በሶማሊያ ተሠማርቶ የቆየው 48ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ተልዕኮውን በውጤት ማከናወኑንም ተናግረዋል።

አባላቱ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) የተሠጣቸውን ግዳጅ በአግባቡ አጠናቆ በመመለሱ በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የ48ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በተሰማሩበት ቀጠና በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የተረጋጋ ሰላም በመፍጠር ግዳጃቸውን ፈፅመው መመለሳቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሶማሊያ የከፈለው መስዋዕትነት ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተረጋጋ ሰላም መፈጠር ሁለንተናዊ ድርሻ እንደነበረውም ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተመላሽ የሠላም አሥከባሪ አባላቱ በቀጣይ በሚሰማሩበት ቦታ የሚጠበቅባቸውን የግዳጅ አፈጻጸም በታማኝነት እና በአገልጋይነት መንፈስ ጀግነትን በመላበስ በአግባቡ መፈፀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

Exit mobile version