Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ በደረሰ የአለት ናዳ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ሰላም ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት አለት ተንዶ በደረሰ አደጋ በውስጡ የነበሩ ሦስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዳስታወቀው፥ አደጋው የተከሰተው ከከፍተኛ ቦታ አለት ተንዶ አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት በማድረሱ ነው፡፡

አደጋው የደረሰው ተጎጂዎች በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እያሉ ሲሆን ፥ በዚህም የሶስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 8 ሰዎች ደግሞ በእሳት አደጋ ሰራተኞች እገዛ መትረፋቸው ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ አደጋዎች እየተከሰቱ በመሆኑ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቅርቧል፡፡

Exit mobile version