አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍቢሲ) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቀው የተማሪዎች ምዘገባ መጀመራቸውን የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮዎች አስታውቀዋል።
በሲዳማ ክልል 1ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ደስታ ገነሜ(ዶ/ር) በበኩላቸው÷ 1 ነጥብ 1ሚሊየን ተማሪዎችን በትምህርት ገበታ ላይ ለማስቀመጥ ምዝገባ ተጀምሯል ብለዋል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መጻህፍትን ለተማሪዎች ተደራሽ መሆኑን የጠቀሱት የትምህርት ቢሮዎቹ ÷የአካባቢ ቋንቋ ትምህርት መጽሃፍት ህትመት ደግሞ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚሰተዋለውን የደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ችግር ለመፍታት በክልሉ መንግስት አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡
በአልማዝ መኮንን