Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጃፓን በከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ከባድ አውሎ ነፋስ መመታቷ ተገለፀ፡፡

በደቡባዊ ጃፓን የተከሰተውን ከባድ አውሎ ነፋስ ተከትሎ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት አራት ሰዎች መሞታቸው የተገለፀ ሲሆን በርካታ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

አውሎ ነፋሱ በሰዓት 252 ኪሎ ሜትር ያካልላል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአካባቢው የተፈጠረው የአየር ሁኔታ የአውሎ ነፋሱን ፍጥነት እያዳከመው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አደጋውን ተከትሎ በደቡባዊ ጃፓን ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት እስካሁን ከ237 ሺህ በላይ ቤቶች የኤሌክትሪክ ሀይል ሲቋረጥባቸው ከ700 በላይ በረራዎች ደግሞ ተሰርዘዋል፡፡

የጃፓን የነፍስ አድን ሰራተኞች ተጎጂዎችን ለማዳን ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version