አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍቢሲ) ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችላቸውን አዲስ የንግድ ምክር ቤት አቋቋሙ፡፡
ምክር ቤቱ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2028 የሚቆይ ሲሆን÷ ሀገራቱ በግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ ቤቶች፣ የምግብ ኢንዱስትሪን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡
የምክር ቤቱ መቋቋምም ሳዑዲ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትብብር የማስፋት ስትራቴጂ አካል ነው መባሉን ዓረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ለማሳደግ መስራት እንደሚጠበቅም መግባባት ላይ መደረሱን ዘገባው አመላክቷል፡፡
የምክር ቤቱ መቋቋም የሀገራቱን የኢኮኖሚ ዕድሎች በመጠቀም ያላቸውን ትብብር ከማጠናከር፣ የንግድ ግንኙነቱን ከማሳለጥና የተቀናጀ የኢኮኖሚ ትስስር አኳያ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ተጠቅሷል።