አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የልማት አጋሮች ሀገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያውን ለማጠናከር የሚውል ተጨማሪ የ3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ቃል መግባታቸው ተገለፀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፌስቡ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ ድጋፉ ለማክሮ ኢኮኖሚ፣ ለመዋቅራዊና ለሴክቶራል ማሻሻያዎች የሚውል ነው።
ይህም የዓለም ባንክ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) 2 ነጥብ 9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ቃል የገቡትን እንደማያጠቃልል ነው የተነገረው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች እና በሳዑዲ ዓረቢያ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚኖሩም ነው የገለፁት።