የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይን አሰናበቱ

By Melaku Gedif

August 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትጵያ ተወካይ አብዱል ካማራን (ዶ/ር) አሰናብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ÷ተወካዩ በ7 ዓመታት ቆይታቸው ለኢትዮጵያ ልማት ላበረከቱት ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡