አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው 5 ሺህ 34 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 34 የላብራቶሪ ምርመራ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መግለፁን ተከትሎ ነው ቫይረሱ የተገነባቸው ከ5 ሺህ በላይ የሆነው።
በ24 ሰዓታት ውስጥም ከተካሄደው አጠቃላይ የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 35 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ሁለት ናሙናዎች ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበቸዋል።
በተጨማሪ አንድ በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበር ሰው ህይወት ማለፉ ነው የተገለፀው።
ህይወታቸው ያለፈውም አንድ ሰው ከአዲስ አበባ እንዲሁም ሁለት ሰዎች ከሶማሌ ክልል ሲሆን በዚህም በኮሮናቫይረስ የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 78 ደርሷል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ወንዶች 113 ሴቶች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸውም ከ6 ወር እስከ 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል ተብሏል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው 186 ሰዎች መካከል 147 ከአዲስ አበባ ፣ 16 ሰዎች ከሱማሊ ክልል ፣ 10 ሰዎች ከአፋር ክልል ፣ 8 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 4 ከኦሮሚያ ክልል እና አንድ ሰው ከደቡብ ክልል ናቸው።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 74 ሰዎች 63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደቡብ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 486 ነው።