አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ኢታንግ ከተማ የሰላምና ልማት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) እና በብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን እየመሩት ነው።
ባለፉት ጊዜያት በአካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች የነበሩ መቃቃሮች አዲስ አመራሮች መሾማቸውን ተከትሎ ሕዝቡ በራሱ ቁርሾዎችን በመተው ሰላሙን በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡