Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ክልሉ የበቆሎ ምርጥ ዘር ፍላጎቱን በራሱ አቅም ለመሸፈን እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት የበቆሎ ምርጥ ዘር ፍላጎቱን ከ50 በመቶ በላይ በራሱ አቅም ለመሸፈን እየሠራ መሆኑን የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ላለፉት ዓመታት የሚያስፈልገው ምርጥ ዘር ከ70 በመቶ በላይ የሚሸፈነው በሌሎች ክልሎች መሆኑን እና ሂደቱም አድካሚ እንደነበር የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና አርሶ አደሩ የሚፈልገውን የበቆሎ ምርጥ ዘር በክልሉ አቅም ለመሸፈን በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ 223 ሄክታር መሬት የምርጥ ዘር ብዜት እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ዓመት የክልሉን የበቆሎ ምርጥ ዘር ፍላጎት ከ50 በመቶ በላይ በራስ አቅም ለመሸፈንና በቀጣይም ሁሉንም የሰብል ዓይነቶች ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን እንደሚሠራ ነው የተገለጸው፡፡

Exit mobile version