Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አፍሪካ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ድጋፉን እንዲቀጥል ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ(ቲካድ ) ድጋፍ ማድረጉን እንዲቀጥል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጠየቁ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የቲካድ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፏል ።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በመድረኩ ÷”ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች” በሚለው መርህ መሰረት ቀጣናዊ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት የአፍሪካን ባለቤትነት እና አመራር ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ለዚህም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የአፍሪካ ጥሩ ተምሳሌት እንደሆነ ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አፍሪካ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረትም የቲካድ ሂደት ድጋፍ ማድረግ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ስብሰባው በ2025 ለሚካሄደው የቲካድ 9 የመሪዎች ጉባኤ የአጀንዳዎች ልየታና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማመላከት የተካሄደ መድረክ ነው።

 

Exit mobile version