Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ሀዘናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ሀዘናቸውን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በመሬት መንሸራተት ወገኖቻችን በመጎዳታቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።

ለብዙ ዘመናት ተፈጥሮን ባለመከባከባችን አሉታዊውን ውጤት እያየነው ነው ሲሉ ገልጸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ በዘላቂነት ችግሩን የመፍቻ ቁልፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሚመለከታቸው አካላት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መመሪያ መሰጠቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ማኅበረሰቡም የተጎዱ ወገኖችን በሚቻለው ሁሉ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version