የሀገር ውስጥ ዜና

በስልጤ ዞን የካሊድ ዲጆ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታን ለማስቀጠል የሚያስችል ጉብኝት ተደረገ

By Feven Bishaw

August 27, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የካሊድ ዲጆ መስኖ ፕሮጀክትን ከተቋረጠበት ለማስቀጠል የሚያስችል ጉብኝት ተደርጓል፡፡

በጉብኝቱ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ ከድር፣ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የጉብኝቱ ዓላማም ተጀምሮ የተቋረጠውን የካሊድ ዲጆ የመስኖ ፕሮጀክትን መልሶ ማስጀመርን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ(ዶ/ር) ለጨረታ የሚያግዙ አስፈላጊ ዝግጅቶች በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በአጭር ጊዜ ተዘጋጅተው ለጨረታ እንዲቀርቡ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡