Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ቡድን የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ሶማሌ ክልል ገባ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ቡድን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ሶማሌ ክልል ገብቷል፡፡

ቡድኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡

የቡድኑ አባላት ሶማሌ ክልል ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የሐይማኖት አባቶች፣ ኡጋሶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ከፍተኛ አመራሮቹ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በመስኖ የለማ የሩዝ ምርትን እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ፡፡

የሩዝ ሰብል የማልማት ንቅናቄ በክልሉ በሸበሌ ዞን ምዕራብ ጎዴ መስኖ ፕሮጀክት በቤርአኖ ባሳለፍነው መጋቢት ወር መጀመሩ ይታወሳል።

በፍሬሕይወት ሰፊው

Exit mobile version