Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግድቡ ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገው ጥረት አመላካች ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጨማሪ ሁለት ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባት ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገው ጥረት አመላካች ነው ሲሉ የቀድሞ የግድቡ ተደራዳሪና የውኃ ኃብት ተመራማሪው ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ገለጹ።

ተመራማሪው ፈቅ አሕመድ ነጋሽ እንደገለጹት፥ የግድቡ ሁሉም ተርባይኖች እስካሁን ወደ ሥራ መግባት የነበረባቸው ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ይህን ማድረግ አልተቻለም።

ቀደም ሲል ወደ ሥራ የገቡት ሁለት ተርባይኖችን ጨምሮ ከሰሞኑ ወደ ሥራ የገቡት ተጨማሪ ሁለት ተርባይኖች የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በእጅጉ እንደሚያሻሽሉ አብራርተዋል።

የግድቡ ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባት የሀገሪቷን የኃይል አቅርቦት ከማሳደግ ባለፈ ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር የምታደርገው ጥረት አመላካች ነው ብለዋል።

በመሆኑም ቀሪዎቹን ተርባይኖች ወደ ሥራ ማስገባት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ መናራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

የሕዳሴ ግድቡ 3ኛ እና 4ኛ ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን ማብሰራቸው ይታወሳል።

Exit mobile version