Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ”ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን” እና ”አዴል” የተሰኙ ፕሮግራሞችን አፈጻጸም እየገመገመ ነው።

በዚሁ ወቅት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር አማካሪ ሞቱማ መቃሳ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማስፋት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው ለአብነትም ”ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን” እና ”አዴል” የተሰኙ ፕሮግራሞች እየተተገበሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘ 625 ዶላር እየተተገበረ በሚገኘው ”ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን” ፕሮግራም ከ10 ሚለየን በላይ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ”አዴል” በተሰኘው ፕሮግራም 5 ሚሊየን ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ 500 ሚሊየን ዶላር በጀት መያዙን ገልጸዋል፡፡

የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን በማስታወስ በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባ አመላከተዋል፡፡

Exit mobile version