አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፔሩ ሊማ የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ዛሬ ሲጀመር ኢትዮጵያ የምትጠበቅባቸው ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ይደረጋሉ፡፡
በዚሁ መሠረት ሌሊት 7 ሰዓት ከ25 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ አትሌት መዲና ኢሳ እና መቅደስ ዓለምእሸት ይጠበቃሉ፡፡
እንዲሁም ሌሊት 7 ሰዓት ከ55 ላይ የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ሲካሄድ÷ አትሌት ንብረት ክንዴ እና አብዲሳ ፈይሳ ተጠባቂ ናቸው፡፡
ከፍጻሜ ውድድሮቹ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ሲካሄዱ÷ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ55 ላይ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት አስቴር አሬሬ ትሳተፋለች።
እንዲሁም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ በሚካሄደው የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ማጣሪያ÷ አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ በተለያየ ምድብ እንደሚወዳደሩ ኢዜአ ዘግቧል፡፡